Songtexte.com Drucklogo

Ye-Fikir Emebet Songtext
von Neway Debebe

Ye-Fikir Emebet Songtext

የፍቅር እመቤት ጓዴ የትዳር የልቤ ሰው
ያንቺን እንጃ በኔስ በኩል ትዝታሽ ልቤን ወረሰዉ
ኧረ ፍቅርሽ ፍቅርሽ አይ ፍቅርሽ
ፍቅርሽ የልቤ ውስጥ እሳት
ይጎዳል ያመነምናል ያደላል ለህመም ለክሳት


የለም ታቂዋለሽ ከጎኔ ሌላ ሰው
ጭንቄን የሚያውቅልኝ ሀሳብ የማወሳው
እርቀሽኝ ምን ልሁን ሳይሽ የማልረካ
እንዲህ ነው የኔ ልብ አምኖ ከተመካ
እንዲህ ነው የኔ ልብ አምኖ ከተመካ
ሆዴስ ማን አለው ልቤስ ማን አለው
አንቺዉ ነሽ መዳኒቱ አትራቂው እቱ
ሆዴስ ማን አለው ልቤስ ማን አለው
ያላንቺም አይሆንለት ተይ እዘኝለት

የፍቅር እመቤት ጓዴ የትዳር የልቤ ሰው
ያንቺን እንጃ በኔስ በኩል ትዝታሽ ልቤን ወረሰው
ኧረ ፍቅርሽ ፍቅርሽ አይ ፍቅርሽ
ፍቅርሽ የልቤ ውስጥ እሳት
ይጎዳል ያመነምናል ያደላል ለህመም ለክሳት


ከልብሽ ቤት ይስራ አይነቃነቅም
እንዳታሳፍሪው ካንቺው ጋር ነው የትም
በደስታ እንደጀመርን በደስታ እንጨርሰው
ይሰማሽ ጭንቀቴ ወይ በይኝ አንቺ ሰው
ይሰማሽ ጭንቀቴ ወይ በይኝ አንቺ ሰው
ሆዴስ ማን አለው ልቤስ ማን አለው
ያላንቺም አይሆንለት ተይ እዘኝለት
ሆዴስ ማን አለው ልቤስ ማን አለው
አንቺዉ ነሽ መዳኒቱ አትራቂው እቱ

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Quiz
Wer singt das Lied „Applause“?

Fans

»Ye-Fikir Emebet« gefällt bisher niemandem.