Songtexte.com Drucklogo

Yewah Libane Songtext
von Aster Aweke

Yewah Libane Songtext

እርም ያጣ ሰውነት እርም ያልፈጠረበት
የማይጨክን ገላ አሞት የሌለበት
ነጋ ጠባ መውደድ የሚቀጥልበት
ስንቱ ነው እንደኔ ቀልቡ የራቀበት
ስንቱ ነው እንደኔ ቀልቡ የራቀበት
አለብኝ ባላንጣ አለብኝ ጠላት
ለአገር የሚያሳጣ ፍቅር የሚሉት
ወይ አልተላመድኩት ሽፍንፍንነቱን
አከናንቦኝ ቀረ ልበ-ቢስነቱን
አዬ...
ግራ ገባኝ እኔስ ጭንቅ አለኝ
ሳላስበው ድንገት አዋለለኝ
ጦሴን ይዞ ይሂድ አልለው
የዋህ ልቤን የትም ሲጥለው
እንዳልታገለው ቀድሞ ይጥለኛል
ከቆንጆ አመልክቶ ፈሰስ ያረገኛል
አሞቴን ፈትኖ ቶሎ ያባባኛል
ልርቅ ያሰብኩትን ያቀራርበኛል
ልርቅ ያሰብኩትን ያቀራርበኛል
ስጋጃውን ንቄ ከአጎዛ ሊያስተኛኝ


ጮማው ከእጄ ገብቶ በዉሃ ሊያከርመኝ
ወርቅ አልማዜን ትቼ ያለ ጌጥ ሊያስኖረኝ
ይህ ልበ-ቢስ ልቤ ከሰው ደጅ ያስቀረኝ
አዬ...
ግራ ገባኝ እኔስ ጭንቅ አለኝ
ሳላስበው ድንገት አዋለለኝ
ጦሴን ይዞ ይሂድ አልለው
የዋህ ልቤን የትም ሲጥለው
እርም ያጣ ሰውነት እርም ያልፈጠረበት
የማይጨክን ገላ አሞት የሌለበት
ነጋ ጠባ መውደድ የሚቀጥልበት
ስንቱ ነው እንደኔ ቀልቡ የራቀበት
ስንቱ ነው እንደኔ ቀልቡ የራቀበት
አለብኝ ባላንጣ አለብኝ ጠላት
ለአገር የሚያሳጣ ፍቅር የሚሉት
ወይ አልተላመድኩት ሽፍንፍንነቱን
አከናንቦኝ ቀረ ልበ-ቢስነቱን
አዬ...
ግራ ገባኝ እኔስ ጭንቅ አለኝ
ሳላስበው ድንገት አዋለለኝ
ጦሴን ይዞ ይሂድ አልልም
የዋህ ልቤን የትም ሲጥለው
አይ...
የዋህ ልቤን የትም ሲጥለው
የዋህ ልቤን የትም ሲጥለው

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Beliebte Songtexte
von Aster Aweke

Quiz
Wer singt das Lied „Haus am See“?

Fans

»Yewah Libane« gefällt bisher niemandem.