Songtexte.com Drucklogo

Sew Hulu Be-hageru Songtext
von Aster Aweke

Sew Hulu Be-hageru Songtext

ዛሬ እናቴ እልሻለሁ ዛሬ ሀገሬ እልሻለሁ ዛሬ
ወገኔ እልሻለሁ ዛሬ ኩራቴ እልሻለሁ ሀገሬ
ዛሬ እንደምን ውለሻል ዛሬ እንደምን አድረሻል ዛሬ
ክፉ ነሽ ደግ ነሽ ዛሬ አረ እንዴት ሆነሻል ሀገሬ

ዛሬ እንቅልፍ አልወሰደኝ ዛሬ አይኔም አልተዘጋ ዛሬ
አዳርሽን ሳልሰማ ዛሬ ሌሊቱም አይነጋ ሀገሬ
እኔ እንዲህ በመናፈቅ እኔ ሆድ እየባሰኝ ዛሬ
በርታ በርታ ብለሽ ዛሬ አለሁልሽ በይኝ ሀገሬ

(እህህህ) እንጀራ ሆነና (እህህህ) የሰው ቁምነገሩ
(እህህህ) አልቀበር አለ (እህህህ) ሰው ሁሉ በሀገሩ
(እህህህ) ልቤ አገሬ ቀርቶ (እህህህ) ብቻዬን ዞራለሁ
(እህህህ) ስቀመጥ ስነሳ (እህህህ) አንቺን አስባለሁ

በልቼ አልጠገብኩም ጠጥቼ ጠምቶኛል
ተኝቼ አላረፍኩም ለብሼ በርዶኛል
ሁልጊዜ እንግዳ ነኝ መንገድ ይጠፋኛል
ከየት ነሽ ጥያቄ ሆዴን ያስብሰኛል
ከየት ነሽ ጥያቄ ሆዴን ያስብሰኛል


ዛሬ ፀሀይ ወጣልሽ ወይ ዛሬ አማርሽልኝ ወይ ዛሬ
ልጆችሽ በጊዜ ዛሬ ሰብሰብ አሉልሽ ወይ ሀገሬ
ዛሬ ይሄን ሁሉ አልፌ ዛሬ ስመጣ ከደጅሽ ዛሬ
ሰላም ጥጋብ ነግሶ ዛሬ እምዬ ላግኝሽ ሀገሬ

እኔ ልሂድ ልሂድ ብዬ እኔ ወንዙን ተሻግሬ ዛሬ
እመጣለሁ እኮ ዛሬ መች ቀረሁ አምርሬ ሀገሬ
ዛሬ መልሰኝ መልሰኝ ዛሬ ስደተኛው እግሬ ዛሬ
ውሰደኝ ውሰደኝ ዛሬ መልሰኝ ሀገሬ ሀገሬ

(እህህህ) እንጀራ ሆነና (እህህህ) የሰው ቁምነገሩ
(እህህህ) አልቀበር አለ (እህህህ) ሰው ሁሉ በሀገሩ
(እህህህ) ልቤ አገሬ ቀርቶ (እህህህ) ብቻዬን ዞራለሁ
(እህህህ) ስቀመጥ ስነሳ (እህህህ) አንቺን አስባለሁ

በልቼ አልጠገብኩም ጠጥቼ ጠምቶኛል
ተኝቼ አላረፍኩም ለብሼ በርዶኛል
ሁልጊዜ እንግዳ ነኝ መንገድ ይጠፋኛል
ከየት ነሽ ጥያቄ ሆዴን ያስብሰኛል
ከየት ነሽ ጥያቄ ሆዴን ያስብሰኛል


ዛሬ እናቴ እልሻለሁ ዛሬ ሀገሬ እልሻለሁ ዛሬ
ወገኔ እልሻለሁ ዛሬ ኩራቴ እልሻለሁ ሀገሬ
ዛሬ እንደምን ውለሻል ዛሬ እንደምን አድረሻል ዛሬ
ክፉ ነሽ ደግ ነሽ ዛሬ አረ እንዴት ሆነሻል ሀገሬ
ዛሬ ፀሀይ ወጣልሽ ወይ ዛሬ አማርሽልኝ ወይ ዛሬ
ልጆችሽ በጊዜ ዛሬ ሰብሰብ አሉልሽ ወይ ሀገሬ
ዛሬ መልሰኝ መልሰኝ ዛሬ ስደተኛው እግሬ ዛሬ
ውሰደኝ ውሰደኝ ዛሬ መልሰኝ ሀገሬ ሀገሬ

(እህህህ) እንጀራ ሆነና (እህህህ) የሰው ቁምነገሩ
(እህህህ) አልቀበር አለ (እህህህ) ሰው ሁሉ በሀገሩ
(እህህህ) ልቤ አገሬ ቀርቶ (እህህህ) ብቻዬን ዞራለሁ
(እህህህ) ስቀመጥ ስነሳ (እህህህ) አንቺን አስባለሁ
(እህህህ) እንጀራ ሆነና (እህህህ) የሰው ቁምነገሩ
(እህህህ) አልቀበር አለ (እህህህ) ሰው ሁሉ በሀገሩ
(እህህህ) ልቤ አገሬ ቀርቶ (እህህህ) ብቻዬን ዞራለሁ
(እህህህ) ስቀመጥ ስነሳ (እህህህ) አንቺን አስባለሁ

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Beliebte Songtexte
von Aster Aweke

Quiz
„Grenade“ ist von welchem Künstler?

Fans

»Sew Hulu Be-hageru« gefällt bisher niemandem.