Songtexte.com Drucklogo

Fikhr Anesgne Songtext
von Aster Aweke

Fikhr Anesgne Songtext

ወፌ ወፌላላ ወፌላላላላ
እስኪ ልጁን እይው ከማን እንደበላ
ጎብኘት አርጊውና ሰፈሩን መንደሩን
ያዋዋሉን ነገር ንገሪኝ አዳሩን
ንገሪኝ አዳሩን
ፍቅር አነሰኝ
ፍቅር አነሰኝ
መውደድ አነሰኝ
ናፍቆት አነሰኝ
ትዝታ አነሰኝ
እንዳከላትህ የት ባደረሰኝ
ዳገት ሸንተረሩን ቆላውና ደጋ
አቀብ ቁልቁለቱን አንተን ፍለጋ አንተን ፍለጋ
ኬሻውን ለብሶ ቢጠቃቅሰኝ
እኔም ወደድኩት ናፍቆት ወረሰኝ
ፍቅር አስለምዶት አካል ሰውነቴን
ሲናፍቀኝ ዋለ ሲበላው አንጀቴን
አንጀቴን አንጀቴን አንጀቴን
ጠረንህ ከራቀ ሀሳብ ከተጠጋኝ
ውሎ አድሯል በኔ ዘንድ መለየት ካሰጋኝ
ዝምታን አወኩታ ትካዜዬ በዛ
ቢርቀኝ ቢጠፋኝ የጨዋታህ ለዛ የጨዋታህ ለዛ
ፍቅር አነሰኝ
ፍቅር አነሰኝ
መውደድ አነሰኝ
ናፍቆት አነሰኝ
ትዝታ አነሰኝ
እንዳከላትህ የት ባደረሰኝ
በህልሜም በውኔም እከተልሃለው
ሌላ አይታየኝም እምልልሃለው እምልልሃለው
ድንጋይ ቢቀብሩት አይበሰብስም
ልቤ አንተን ወዶ አልተመለሰም
ፍቅር ለብቻ ከሚያስገድደኝ
እስኪ ስወድህ አንተም ውደደኝ
ውደደኝ ውደደኝ
Jetzt Songtext hinzufügen

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Beliebte Songtexte
von Aster Aweke

Fans

»Fikhr Anesgne« gefällt bisher niemandem.