Songtexte.com Drucklogo

Alèm Shègga Songtext
von Asnaqètch Wèrqu

Alèm Shègga Songtext

አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ
ሳስብህ አድራለሁ አንተን ሳሰላስል
ሀሳብ በውለታ ይቆጠር ይመስል

አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ
አዲሱን ቀሚሴን እሳት ፈጀው ማታ
ፍቅሬ ያንተን ነገር ስቋጥር ስፈታ

አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ
ከማዉጣት ከማውረድ ዘላለም ከማሰብ
ላርግህ ከደረቴ እንደ ልሳነ ሰብ


አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ
አሎድሽም በለኝ ልቤ ተጨነቀ
መጥላትም ፍቅር ነው ቁርጡ ከታወቀ

አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ
ደናደሪ ብሎ እጄን ቢጨብጠው
ተበጠስኩኝ ደክር ሟሟሁኝ እንደ ጨው

አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ
እስቲ ዝም በሉት ሠው ይነጋገራል
መጨነቄን አውቆ መቶልኝ ይሆናል

አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ
አወጣጥህ መልካም ቡቃያህ ማማሩ
አንተ አይደለህም ወይ የትዝታ ዘሩ

አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ
አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Beliebte Songtexte
von Asnaqètch Wèrqu

Quiz
Welcher Song kommt von Passenger?

Fans

»Alèm Shègga« gefällt bisher niemandem.