Songtexte.com Drucklogo

Marign Biyeshalo Songtext
von Alemayehu Eshete

Marign Biyeshalo Songtext

አንዱን አካል ፍቅር መለየት ገንጥሎት
አለው በግማሹ ደስታን ሀዘን ጥሎት ...አሀሀ

በደስታ ሀዘን በሳቅ ፈንታ ለቅሶ
የምሩን ፍቅር በንባ ተለውሶ... አሀሀ

ማሪኝ ብዬሻለው እሞትብሻለው
የአስታራቂ ያለ እርዱኝ እባካችሁ
ብቸኛ ፍቅሬን አምጡልኝ ይዛችሁ... አሀሀ

የአጋጣሚ ነገር ወይ ቀነ ጎዶሎ
ልቤን አሸፍቶ በንዋይ ተታሎ


ማሪኝ ብዬሻለው እሞትብሻለው
ሰው ሆኖ ስህተትን የማይሰራ የለም
የአንድ ቀን ጥፋቴን ማሪኝ ተይ ግድ የለም.አሀሀ

በደሌን እረስተሽ ማርኩህ በይኝ ፍቅሬ
በናፍቆት ሰንሰለት እንዳልኖር ታስሬ.አሀሀ

ማሪኝ ብዬሻለው እሞትብሻለው

...ቆዳዬ ተገፉ ይሁንልሽ ጫማ
ስጋዬም ይደገም ላንቺ ከተስማማ... አሀሀ

አጥንቴን ይብረደው እራቁቴንም ልሂድ
ከአንቺ የበለጠ አላገኝም ዘመድ... አሀሀ

ማሪኝ ብዬሻለው እሞትብሻለው

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Beliebte Songtexte
von Alemayehu Eshete

Fans

»Marign Biyeshalo« gefällt bisher niemandem.