Songtexte.com Drucklogo

Maebel New Songtext
von Neway Debebe

Maebel New Songtext

ማእበል ነው ማእበል ነው ፍቅሯስ
የባህር ላይ የውቂያኖስ ንፋስ
ወይ አልወቅሰው ወይ አልከስ እንድካስ
አይነገር አይወራ የሷስ

ማእበል ነው ማእበል ነው ፍቅሯስ
የባህር ላይ የውቂያኖስ ንፋስ
ወይ አልወቅሰው ወይ አልከስ እንድካስ
አይነገር አይወራ የሷስ

ወዶ የገባ ሰው ከባህር ከውሀው
ዋኝቶ ይውጣው እንጂ ሌላ ማን ሊረዳው
የተፈጥሮ ቅርጿ ስቦኝ ዘፍቂያለሁ
የውቂያኖስ አሳ ምርኮኛ ሆኛለሁ

ሞገደኛው ያ ሀይለኛው ፍቅሯ ሸብቦ ሸብቦ
ከባህር ውስጥ ከውቂያኖስ የዘፈቀኝ ስቦ
ሊያስቀረኝ አስቦ
እሷን እሷን ሁለት እጇን ይዛችሁ ጠይቋት
ዋናተኛ ጠላቂ ሰው ከሆንሽ አውጪው በሏት


ሰፍ ሰፍ
ማእበል ፍቅሯ ሰፍ ሰፍ
ወስዶ ሲያንሳፍፍ ሰፍ ሰፍ
ማእበል ፍቅሯ ሰፍ ሰፍ
የሚያክነፈንፍ ሰፍ ሰፍ
ማእበል ፍቅሯ ሰፍ ሰፍ
አይ ሲያስለፈልፍ ሰፍ ሰፍ
ማእበል ፍቅሯ ሰፍ ሰፍ

እንዳውሎ ንፋስ የሚወረወር
የልብ አድርሶ ካይን የሚሰወር
መች ያስታውቃል ፋታም አይሰጥም
እያሳሳቀ ወስዶ ሲያሰጥም
እንደ ማእበል የባህር ሞገድ
ፍቅሯ ማርበድበድ ማስጨነቅ ሲወድ
ሆሆሆይይይ ማእበል

ማእበል ነው ማእበል ነው ፍቅሯስ
የባህር ላይ የውቂያኖስ ንፋስ
ወይ አልወቅሰው ወይ አልከስ እንድካስ
አይነገር አይወራ የሷስ

ማእበል ነው ማእበል ነው ፍቅሯስ
የባህር ላይ የውቂያኖስ ንፋስ
ወይ አልወቅሰው ወይ አልከስ እንድካስ
አይነገር አይወራ የሷስ

ያአይኖቿ ብርሀን ፀሀይ የመሰለ
ማቃጠል ጀምሯል ወንድ እየነጠለ
በጥቅሻ ቋንቋ ታተራምሳለች
ባይኖቿ መናገር ቅኔ ጀምራለች


አይበገር አይሸነፍ ፍቅሯ አያደርግ የለ (አይኔ)
የኔስ ነገር የኔስ ጉዳይ ለታምር ታደለ
ልቤ እየዋለለ
ማእበል ነው ውሽንፍር ነው ንፋስ አዘል ሞገድ
ሀያል ፍቅሯ ያሸንፋል ይጥላል ከወጥመድ

ሰፍ ሰፍ
ማእበል ፍቅሯ ሰፍ ሰፍ
ወስዶ ሲያንሳፍፍ ሰፍ ሰፍ
ማእበል ፍቅሯ ሰፍ ሰፍ
የሚያክነፈንፍ ሰፍ ሰፍ
ማእበል ፍቅሯ ሰፍ ሰፍ
አይ ሲያስለፈልፍ ሰፍ ሰፍ
ማእበል ፍቅሯ ሰፍ ሰፍ

እንዳውሎ ንፋስ የሚወረወር
የልብ አድርሶ ካይን የሚሰወር
መች ያስታውቃል ፋታም አይሰጥም
እያሳሳቀ ወስዶ ሲያሰጥም
እንደ ማእበል የባህር ሞገድ
ፍቅሯ ማርበድበድ ማስጨነቅ ሲወድ
ሆሆሆይይይ ማእበል

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Quiz
„Grenade“ ist von welchem Künstler?

Fans

»Maebel New« gefällt bisher niemandem.