Songtexte.com Drucklogo

Alfual Songtext
von Abdu Kiar

Alfual Songtext

የላይ ላዩን ብቻ እያያችሁ
የላይ ላዩን ብቻ እያያችሁ
ተመችቶታል አትበሉኝ
የኔ ነገር መቼ ገባችሁ
ያጣሁትን ማን አወቀልኝ
ጉዳቴንስ ማን ተረድቶታል
ፍቅር ፍቅር ይላል ገላዬ
ብቸኝነት አስጠልቶታል

በልቼ ጠጥቼ ኖርኩኝ ሊባል ነው ወይ
አለመፋቀሬ ውርደት አይደለም ወይ
ፍቅር የለሽ ኑሮ - ኑሮ ከተባለ
ABD ከእንስሳ በምኑ ተሻለ!

ለኔ ያለልኝን ለኔ ያለልኝን
እድሌን ልጠብቅ እሱ የመረጠልኝን
ለኔ ያለልኝን ለኔ ያለልኝን
እድሌን ልጠብቅ እሱ የመረጠልኝን


በልቼ ጠጥቼ ኖርኩኝ ሊባል ነው ወይ
አለመፋቀሬ ውርደት አይደለም ወይ
ፍቅር የለሽ ኑሮ - ኑሮ ከተባለ
ABD ከእንስሳ በምኑ ተሻለ!

ባዶ ቤቴ ያ ባዶ ቤቴ ሙሉ መስሎ የሚታያችሁ
ፍቅር ና ደስታን እንዳጣ አፍ በኖረው በነገራችሁ
ያለ ፍቅር ያለ ፍቅረኛ ለብቻዬ እየኖርኩበት
ተመችቶታል አትበሉኝ የኔ ኑሮ መከራ አለበት

በልቼ ጠጥቼ ኖርኩኝ ሊባል ነው ወይ
አለመፋቀሬ ውርደት አይደለም ወይ
ፍቅር የለሽ ኑሮ - ኑሮ ከተባለ
ABD ከእንስሳ በምኑ ተሻለ!

ለኔ ያለልኝን ለኔ ያለልኝን
እድሌን ልጠብቅ እሱ የመረጠልኝን
ለኔ ያለልኝን ለኔ ያለልኝን
እድሌን ልጠብቅ እሱ የመረጠልኝን

በልቼ ጠጥቼ ኖርኩኝ ሊባል ነው ወይ
አለመፋቀሬ ውርደት አይደለም ወይ
ፍቅር የለሽ ኑሮ - ኑሮ ከተባለ
ABD ከእንስሳ በምኑ ተሻለ!

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Beliebte Songtexte
von Abdu Kiar

Ähnliche Artists

Fans

»Alfual« gefällt bisher niemandem.